የማህበሩ ራዕይ፤ ተልዕኮ እና ቁልፍ ተግባራት

የማኅበሩ ራዕይ

የአምባ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር አባላት የሚተማመኑበት፣ ቁጠባንና ኢንቬስትመንትን በማበረታታት ለማህበራዊና እኮኖሚያዊ ዕድገታቸዉ አስተማማኝ የገቢና የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ ማየት ነዉ፡፡

የማኅበሩ ተልዕኮ

የአምባ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ተልዕኮ የአባላትን ዕዉቀት፣ ልምድ፣ ጉልበት እና ገንዘብ/ሀብት/ በማቀናጀት በጋራ የሥራ ካፒታልን በመፍጠር ገቢያቸዉን ለማሳደግና ለፕሮጀክቶቻቸዉ የፋይናንስ ምንጭ በመሆን የኢኮኖሚ አቅማቸዉንና ፍላጎታቸዉን ማሟላት ነዉ፡፡

የማህበሩ አጠቃላይ ቁልፍ ተግባራት

በማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብ መሰረት ተጨማሪ አባላትን በመጋበዝና የነባሮችን የቁጠባ አቅም በማሳደግ የቁጠባ፤ የሼር ሽያጭ እና ሌሎች የገቢ ምንጮችን በመጨመር የዉስጥ የፋይናንስ አቅምን ማጎልበት፤ ማህበሩ ከራሱ እና ተጨማሪ የፋይናንስ ምንጮችን በማፈላለግ ለአባላቱ እና ለሌሎች ማህበራት የብድር አገልግሎት በመሰጠት ለፕሮጀክታቸዉ የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ፤ አባላት የተበደሩትን ገንዘብ አዋጭነት ባለዉ ሥራ ላይ እንዲያዉሉ የምክርና ሥልጠና አገልግሎት እና ሌሎች አስፋለጊ ድጋፎችን መስጠት፤ ዘመናዊ የፋይናንስና የብድር አስተዳደር ሥርዓት በማስፋፋት በዉጤቱም የአባላትን ተጠቃሚነት ማሳደግ፤ የማህበሩን ትርፋማነት በመጨመር ለአባላት ገቢ መጨመር ብሎም ለአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ፤ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ለማኅበሩ ዕድገት የሚጠቅሙ የንግድ ሥራዎችን መሥራት፤